+251-11-551-7080

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በግብርና ንግድ ላይ ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠር የሚያስችል ፕሮ- አግሮ ኢትዮጵያ የተሰኝ አዲስ ፕሮጀክትን ለመተግበር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ተገቢና ምቹ የሥራ እድል መፍጠር የሚያስችል ፕሮ- አግሮ ኢትዮጵያ የተሰኝ አዲስ ፕሮጀክትን ለመተግበር የመግባቢያ ሰነድ ህዳር 18/ 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ከአለም የስራ ድርጅት ጋር ተፈራረመ፡፡
በፊርማ ስነ-ስራዓቱ ላይ የጅቡቲ፣የሱማሊያ፣የሱዳን እና የደቡቡ ሱዳን የአለም ሥራ ድርጅት ጽ/ቤት ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ህብረትና እና የኢ.ሲ.ኤ. ተወካይ ክቡር አቶ አሌክሲዮ ሙሲንዶ ፕሮጀክቱ በአማራና በደቡብ ክልሎች በ5 ሚሊዮን ዩሮ ለ42 ወራት የሚተገበር እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ሴቶችና ወጣቶች ሥራ ዕድል ፍጠራ ስልጠና እንዲወስዱና በተለዩና አዋጭ በሆኑ የግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር፤ የገበያ ትስስር በመፍጠር ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ የሚስያስችል እንደሆነ በወቅቱ ገልጸዋል፡
ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር በበኩላቸው የፕሮጀክቱ ትግበራ ውጤታማ እንዲሆን የብዙ ተቋማትን ትብብርና ቅንጅት የሚጠይቅ በመሆኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ሌሎች ሴክተሮችም ጋር ሚኒስቴር መስሪያ-ቤታቸው ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋገግጠዋል፡፡
ክቡር አቶ መላኩ አለበል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር በተመሳሳይ ፕሮጀክቱ ለሴቶችና ወጣት ዜጎች በግብርና ንግድ ዘርፍ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል በመሆኑ ከአለም የሥራ ድርጅት እና ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ሚኒስቴር መስሪያ-ቤታቸው በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ8.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ለገሰ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች ያገኘውን ግምታቸው ከ8.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ ከ400 በላይ የሆኑ ዊልቸሮችን፣ ከዘራ፣ ክራንችና የእጅ መደገፊያ ፣ ዘይት፣ ዱቄት ፣ፓስታ፣ መኮረኒ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች ማክሰኞ ህዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም አከፋፍሎል፡፡
ከተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ 5 ሚሊዮን ብር ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተገኘና ለሴክተሮችና ለአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ለቁሳቁስ ግዥ የዋለ መሆኑ በወቅቱ ተጠቅሶል፡፡
መቀመጫውን አሜሪካ ሀገር ካደረገው አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ያገኘውን ግምቱ 3.3 ሚሊዮን ብር የሚሆን ከ400 በላይ ብዛት ያላቸው ዊልቸሮች፣ ከዘራ፣ ክራንችና የእጅ መደገፊያ ቁሳቁሶች ለአማራ፣ ለኦሮሚያ፣ ለቢኒሻንጎል፣ ለጋምቤላ፣ ለአፋር፣ ለሲዳም ክልሎች እና ለሁለት ከተማ አስተዳደሮች ርክክብ ተደርጓል፡፡
በርክክብ ሥነ-ሥራዓትቱ ላይ ክብርት ደ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ ኮሮና ወረርሽን እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ጉዳት በመገንዘብ ችግሩን በዘላቂነት ለመቋቋምና ለመቀነስ ዩኒሴፍ ላደረገወው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
አጋቤ ላደረገውም ድፋፍም ምስጋና አቅርበወ የኮሮና ወረርሽን ከአገራችን ሙሉ ለሙ እስኪጠፋ ድረሰ መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሚኒስቴሯ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ሚስተር ቪንቶስ ቪንሲን የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ተወካይ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ መንግስት ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
ዩኒሴፍ በዚህ ረገድ ድጋፍ እንደያሚደርግና በተለይም ህጻናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶችን ማገዝ የሚያስችል ድጋፎችን ያደርጋል ብለዋል፡፡
Close Menu
Font size
Colors