+251-11-551-7080

ምቹ የሥራ ሁኔታና ማህበራዊ ጥበቃ ለሁሉም!

MOLSA

To see Ethiopia that created enough productive employment and settled decent work situation 

MOLSA In Action

ህዳር 24 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም.አዲስ አበባ- በየዓመቱ ህዳር 24 ቀን የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በጋራ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በዓሉ ‹‹አካል ጉዳተኞችን አካታች፣ ምቹና ዘላቂ የተሻለ ዓለምን በድህረ ኮቪድ-19 እንገንባ!›› በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ለ28ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ29ኛ ጊዜ እየተከበረ ሲሆን ለመሪ ቃሉ ተግባራዊ ምላሽ መስጠት በሚያስችል መልኩ የአካል ጉዳተኞችን የእኩል ዕድል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ተገልፆል፡፡
የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በመሪ ቃሉ የተካተቱ አካል ጉዳተኞችን የሚያካተት፣ ምቹ መደላድል የሚፈጥር እና በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርአት መዘርጋት፤ በተግባርና በተጨባጭ ልናሳይ ይገባል ብለዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የአካል ጉዳተኛ ዜጐች መብቶችና ጥቅሞች እንዲከበሩ ዘርፈ ብዙ ጥረት እያደረገ ሲሆን ብሔራዊ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ ፣ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት መብትና ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮንቬንሽን አዋጅ ፣ ብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች የድርጊት መርሃ ግብርና የአካላዊ ተሐድሶ ስትራቴጂ፣ ለአካል ጉዳተኞች ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪ የማስገባት መመሪያ ወጥቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜም በአካል ጉዳተኞች የመብት ጥሰት ለመከላከልና የእኩል ዕድል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዘውን ‹‹የተጠቃለለ የአካል ጉዳተኞች ሕግ›› በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡
 
 
ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር ለሚሄዱ ዜጎች መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል “የጉዞ ስንቅ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያም ይፋ ተደረጓል፡፡
ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ፡ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዓለም የሥራ ድርጅት ጋር በመተባበር የሥራ ገበያ ዳሰሳ አውደ ጥናት አካሄዷል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት የሥራ ገበያ ዳሰሳ ጥናቱ ለሀገራችን ዜጎች በስራ ምክንያት ለሚሄዱባቸው አረብ ሀገራት የሚገኙ የስራ ገበያ አዝማሚያዎችና እድሎችን ለመለየት የሚያስችል በመሆኑ ፋይዳው የላቀ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በአውደ ጥናቱ ላይ ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር ለሚሄዱ ዜጎች መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል በእንግሊዘኛ፣ በአማርኛ፣ በኦሮሚኛና በትግረኛ የተዘጋጀ “የጉዞ ስንቅ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደርጓል፡፡
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያገኘውን ግምታቸው ከ8 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
በዚህም ከ400 በላይ የሆኑ ዊልቸሮችን፣ ከዘራ፣ ክራንችና የእጅ መደገፊያ፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ፓስታ፣ መኮረኒ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች አከፋፍሏል፡፡
ከተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ 5 ሚሊየን ብር ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተገኘ ሲሆን ይህም ለሴክተሮችና ለአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ለቁሳቁስ ግዢ የዋለ መሆኑ ተገልጿል፡፡
መቀመጫውን አሜሪካ ሀገር ካደረገው አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘውን ግምቱ 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሆነውን ድጋፍ ለአማራ፣ ለኦሮሚያ፣ ለቢኒሻንጉል፣ ለጋምቤላ፣ ለአፋር፣ ለሲዳማ ክልሎች እና ለሁለት ከተማ አስተዳደሮች አስረክቧል፡፡

የሚኒስቴር መ/ቤታችን ባለድርሻ አካላት

ባለድርሻ አካላት ከተለያዩ የሚኒስትር መ/ቤቶች

መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ፌዴሬሽኖች፣ኮንፌዴሬሽንና ሲቪክ ማህበራት

Close Menu
Font size
Colors