በስራ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችንና የሙያ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ መንግስት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡

በኢትዮጵያ በስራ ላይ አደጋና የሙያ በሽታዎች ምዝገባና ሪፖርት ሥርዓት ያሉበትን ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ምክክር አውደ ጥናት ተካሄዷል፡፡
****************************************

ታህሳስ 15 ቀን2013 ዓ.ም አዲስ አበባ፡ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና አጠባበቅ ት/ቤት ጋር በመተባበር የሀገሪቱ የሥራ ላይ አደጋዎችና የጤና ጉዳቶች ምዝገባና ሪፖርት ሥርዓት ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ከመከለስ አኳያ ያሉበትን ተግዳሮቶች በመለየትና ቀጣይ ማሻሻያዎችን ማካሄድ እንዲቻል የግማሽ ቀን የፖሊሲ ምክክር አውደ ጥናት ተካሄዷል፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት ሚኒስቴር መ/ቤቱ በስራ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችንና የሙያ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ መንግስት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ቢገኝም በአፈጻጸም ረገድ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እንዲቻል በቅንጅት የመስራት፣የአቅም ክፍተቶችን የመሙላትና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን ላይ ትኩረት ተስጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በምክክር አውደ ጥናቱ በኢትዮጵያ በስራ ላይ አደጋ፣ የሙያ በሽታዎች ምዝገባና ማስታወቂያ ሥርአት ያሉበትን ተግዳሮቶችና የወደፊት ተስፋዎችን መሰረት ያደረገ የጥናት ሪፖርት በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀርቧል፡፡በተመሳሳይ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍ የሚስተዋለውን የሙያ በሽታዎችና ጉዳቶች ተጋላጭነት ላይ ያተኮረ የጥናት ሪፖርትም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና አጠባበቅ ትምህርት ቤት እጩ ዶ/ር በሆኑት በአቶ ይፎክር ተፈራ ቀርቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Font size
Colors