ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸው የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ አበበን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የምዕራብ እዝ መከላከያ ሆስፒታል እና የልዩ ሀይል የቁስለኞች ማቆያ በመገኘት በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት በመጎብኘት አበረታተዋል፡፡

በሕግ ማስከበር ሀገራዊ ተልዕኮው ወቅት ለደረሰው የአካል ጉዳት ድጋፍ እንዲሆን ለሆስፒታሎቹ የዊልቸር፣ ክራንች እና ዎከር ድጋፍም ተደርጓል፡፡

በተያያዘ ዜናም በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ይኖሩበት የነበረውና የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ሆፃናት አምባን ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑ ታውቋል፡፡

ለሀገር የዋሉ ጀግኖች ማግኘት የሚገባቸውን ክብርና ትኩረት ወደጎን በማለት የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ ከለውጡ በፊት በነበረው ስርዓት አገልግሎት እንዲያቆም በመደረጉ በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ለሀገር ያበረከቱትን ውለታ የዘነጋ ተግባር ሲፈፀምባቸው ቆይቷል፡፡

በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ይኖሩበት የነበረውና የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባን ለማቋቋም በበጎ ፈቃደኝነት የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ አደራጅ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን ኢንጂነር አዳሙ አንለይ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ መቋቋም ለሀገር ክብር ዘብ በመቆም እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለከፈሉና እየከፈሉ ላሉ ጀግኖችና ወላጆቻቸውን መስዋት ላደረጉ የጀግኖች ልጆች ተገቢውን ቦታ እና ክብር መስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Font size
Colors