ግምቱ ከ5ዐ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የምግብ፣ የአልባሳት እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች ተደረገ

ግምቱ ከ5ዐ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የምግብ፣ የአልባሳት እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች ተደረገ


የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ያሰባሰበውን ግምቱ ከ5ዐ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የምግብ፣የአልባሳት እና የቁሳቁስ ድጋፍ በትግራይ፣ በመተከል እና በአጣዬ ለተፈናቀሉና በተለያዩ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ ዜጎች እንዲውል ድጋፍ ተደረገ፡፡ ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር የተሰበሰበውን ድጋፍ አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ግምቱ ከ5ዐ ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን 137 ሺ ኪሎ ግራም የሚመዝን የምግብ፣ የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከተሰበሰበው 137 ሺ ኪሎ ግራም ውስጥ 66 ሺ ኪሎ ግራም ለትግራይ፣ 36 ሺ ኪሎ ግራም ለመተከል እና 35 ሺ ኪሎ ግራም ለአጣዬ ከተማ ለተፈናቀሉና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር ውሰጥ ላሉ ዜጎች ከዛሬ ጀምሮ እንደሚከፋፈልና በየመዳረሻ ቦታዎች እንደሚደርስ ተናግረዋል፡፡
ክብርት ሚኒስቴሯ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴውን፣ ድጋፍ ያደረጉ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን አመስግነው፤ ለተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር የተጋለጡ ዜጎችን የመደገፍ፣ የመረዳት ፣ካሉበት ችግር እንዲወጡ እና ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ የሁሉም ዜጋና ተቋም ኃላፊነት በመሆኑ ሁሉም ሊተባበርና የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Font size
Colors