ሚኒስቴር መ/ቤቱ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብር በይፋ ጀምሯል፡፡

ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ፡ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገር አቀፍ በጎ አድራጎት እንቅስቃሴ አካል በመሆን የአቅመ ደካሞችን ቤት ዕድሳት በዛሬው ዕለት በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ ስምንት በይፋ አስጀምሯል፡፡የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እድሳቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት፤ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች የማደሱ ስራ አቅም በፈቀደ መጠን ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር በቅንጅት በመሆን የሚከናወን ይሆናል ብለዋል።በመርሃ ግብሩ ላይ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በእለቱም የ4 ቤቶችን እድሳት አስጀምረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Font size
Colors